ንግድ ሲጀምሩ በሂሳብ አያያዝ እና በክፍያ መጠየቂያ ማውጣት ከየት እንደሚጀምሩ ማወቅ ከባድ ሊሆን ይችላል። ክፍያ ማግኘት ስለሚፈልጉ የክፍያ መጠየቂያ ማውጣት እጅግ አስፈላጊ ቢሆንም የሂሳብ መዛግብትዎን ለመያዝም አስፈላጊ ነው። ለደንበኞች የክፍያ መጠየቂያ መላክ እንደዛሬው ቀላል ሆኖ የማያውቅበት ዘመን ላይ እንገኛለን፤ አሁን ለአብዛኞቹ ስማርት ስልኮች የክፍያ መጠየቂያ መተግበሪያዎችን እንኳ ማግኘት ይችላሉ። ቀላል እንዲሆኑ እና ደንበኞች ሊከፍቱት በሚችሉት ቅርጸት መሆናቸውን ማረጋገጥዎን ያስታውሱ።
የክፍያ መጠየቂያ ማውጣት መቼ መጀመር አለብኝ?
መልሱ፦ ወዲያውኑ ነው። የመጀመሪያውን ምርትዎን እንደሸጡ የክፍያ መጠየቂያ ይፍጠሩ። መጀመሪያ ላይ ከግብር ገደቦች በላይ የሚያደርስዎ ገቢ እንደሚያገኙ ባይገምቱም አንድ ቀን የሂሳብ መዛግብትዎን መለስ ብለው መመርመር ያስፈልግዎታል፤ ስለዚህ ከመጀመሪያው መዛግብትን መያዝ ግድ ነው። ትናንሽ ግብይቶችም ቢሆኑ የክፍያ መጠየቂያ ሊወጣላቸው ይገባል፤ ይህም በረጅም ጊዜ የሂሳብ አያያዝዎን ያቀልልዎታል።
አስተያየቶች
እስካሁን ምንም አስተያየት የለም።